በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከ286 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተነግሯል፤ በበጀት ዓመቱ 493 ሺህ 497 የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ነበር፡፡ ከስድስት ወራት ታዲያ ለ286ሺህ 139 የሥራ ዕድል ሊፈጠር ችሏል ነው የተባለው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 34 ሺህ 394 ለሚሆኑት በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ናቸው፡፡ አጠቃላይ አፈጻጸሙም 57 ነጥብ 98 በመቶ ሆኗል፡፡
ክልሉ ካለበት የሥራ ፈላጊ ጫና ሲታይ ከዕቅድ አኳያ ግቡን መትቷል ማለት እንደማይቻል የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል፡፡ የሥራ አጥነት ችግር በክልሉ እጅግ አሳሳቢ የማክሮ ኢኮኖሚ ችግርና ውጤቱም ማሕበራዊ ቀውስ የሚያስከትል በመሆኑ በቂ ትኩረት ሊሰጠው ይገባልም ብለዋል፡፡
(ሳባ ሙሉጌታ)
በኲር የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም