ድርጅታችን መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዮን ኃ.የተ ጀንፈል ቀይ እና ነጭ ሩዝ ብዛት 2,535 ኩ/ል፣ ሽንብራና ጓያ ብዛት 97 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በዚህ ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ከመገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዮን ኃ.የተወሰነ ገዝቶ በመውሰድ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን ሰነዶች አሟልተው እና ዋጋቸውን ሞልተው በፖስታ በማሸግ ከዩኒዬኑ ጽ/ቤት ደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታዎቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ጨምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ7ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፤ ሆኖም ግን 7ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የምርቱን ናሙና ማየት ለሚፈልጉ በዩኒዮኑ መጋዘን ደ/ታቦር ኢንዱስትሪ መንደር ካለው መጋዘን ማየት ይቻላል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ የሞላ (ያቀረበ) ሲሆን አሸናፊው በተለየ በ5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ (ሲፒኦ) በማስያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡
- ዩኒዮኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ምርቱን የሚረከበው ከዩኒዮኑ መጋዘን ሲሆን የትራንስፖርት እና የወዛደር ማስጫኛ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተወሰነ