አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት፣ በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ለስራ ሲጠቀምባቸው የነበሩ በማህበሩ ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- መግዛት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 እና በአዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡትን ተሽከርካሪዎች ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሠነዱ ላይ በማየት በማህበሩ ዋናው መ/ቤት እና አዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት በአካል ተሽከርካሪዎችን በማየት ዋጋውን በዋጋ መሙያው ቅጽ መሠረት ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላትና በፓስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የተሸከርካሪ ዋጋ ከመነሻ ዋጋ ማነስ የለበትም፡፡ ከመነሻ ዋጋ በታች ዋጋ የሞሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከማህበሩ ጋር አስፈላጊውን የውል ስምምነት በመፈፀም ውል ከያዙበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አሰር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)

