ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
76

የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንኡስ አንቀፅ 1 መሠረት በ2017 በጀት አመት 1ኛ ዙር በመደበኛ ጨረታ ለመኖሪያ 21 ፣ ለድርጅት 4 አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሠው ወይም ድርጅት ከ19/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 07 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30  እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 07 ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ አስተዳደር አዳራሽ ይሆናል፡፡
  5. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 07 07 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ቦታውን ለመጐብኘት የሚፈልግ አካል በ20/05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ከተማ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት ከኮሚቴው ጋር በመገናኘት መጐብኘት ይቻላል፡፡

የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here