ልብ የራሱ አንጐል አለዉ

0
113

በልብ ውስጥ ምትን ወይም ትርታን የሚቆጣጠር የደም ስር ስርዓት የተዘረጋበት ትንሽ አንጐል እንደሚገኝ ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል::

በስዊድን የካሮሊንስካ ተቋም እና የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በጋራ ባደረጉት አዲስ ጥናት በልብ ውስጥ ምትን የሚቆጣጠር የራሱ የነርቭ ስርዓት የተዘረጋበት አንጐል እንደሚገኝ ደርሰውበታል::

ከዚህ ቀደም የልብ ምት ቁጥጥር የሚካሄደው በጭንቅላት ውስጥ ባለ አንጐል በሚተላለፍ መልእክት ነው ተብሎ ነበር የሚታሰበው:: በልብ የላይኛው ክፍል የሚኘው የነርቭ ስርዓትም በጭንቅላት ውስጥ ካለው አንጐል የሚወጣን መልእክት የማስተላለፍ ቀላል ሚና እንደነበረው ነበር የሚታመነው:: ይሁን እንጂ በቅርቡ የተደረጉ ጥናትና ምርምሮች የላቀ ተግባር ያለው መሆኑን አመላክተዋል::

ጥናት እና ምርምሩን የመሩት በስዊድን የካሮሊነስካ ተቋም ኒውሮ ሳይንስ ዳይሬክተር ኮንስታንቲኖስ አፓትስ በልብ የላይኛው ክፍል ያለው ትንሽ አንጐል በራስ ቅል ውስጥ ከሚገኘው አንጐል እንቅስቃሴ እና የመተንፈሻ አካላትን ከሚቆጣጠረው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ነው ያብራሩት::

ተመራማሪዎቹ በልብ ውስጥ የሚገኘው የነርቭ ስርዓት ውስብስብ መሆኑን አረጋግጠዋል:: የተለያዩ ተግባራትን የሚከውኑ የነርቭ ህዋሳትንም ለይተዋል:: የነርቭ ስርዓቱን ውስብስብነት መረዳት መቻላቸው በቀጣይ ስለልብ በሽታዎች አዳዲስ ግንዛቤን ጨብጠው መድሃኒት በማግኘት እንደሚያስችላቸው ነው የቡድን መሪው ኮንስታቲኖስ ያብራሩት::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የታኅሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here