ሎካ አባያ ብሔራዊ ፓርክ

0
55

በኢትዩጵያ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰብ እና ህዝቦች በሲዳማ ክልል አባይ ወረዳ ነው የሚገኘው- ሎካ አባያ ብሔራዊ ፓርክ::

ፓርኩ ከአዲስ አበባ 340 ከአዋሳ ደግሞ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የተመሰረተው::

ሎካ አባያ ብሔራዊ ፓርክ በአባያ ኃይቅ እና በብላቴ ወንዝ መካከል ነው የሚገኘው:: ጠቅላላ ስፋቱም 500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ተለክቷል:: በመልካ ምድራዊ አቀማመጡ ኮረብታዎች፣ የሳር ምድር፣ ጥቅጥቅ ደን እና የብላቴ ወንዝ ተፋሰስ ስነ ምህዳርን  አካቶ ይዟል::ከፓርኩ ክልል ከፍተኛው የጉዳኖ ኮረብታ 1650 ሜትር፤ ዝቅተኛው ሻላ ኦዳ 1178 ሜትር ተለክቷል::

በፓርኩ ክልል 198 የእፅዋት ዝርያዋች፣ 28 መካከለኛ እና በአካል ግዝፈት ያላቸው አጥቢ የዱር እንስሳት እና ከ200 በላይ የዓእዋፍ ዝርያዎች መገኘታቸው ተመዝግቧል- በድረ ገፆች::

ከዱር እንስሳትም አንበሳ፣ አቦ ሸማኔ፣ ጉማሬ፣ የዱር ውሻ፣ ዓዞ፣ መገኘታቸው ተረጋግጧል::

በዓየር ንብረቱ በረሀማ እና ወይና ደጋ ሲሆን አማካይ ሙቀቱ 16 ዲግሪ ሴልሺየስ ተለክቷል::

ሎካ አባያ ብሔራዊ ፓርክ የዱር እንስሳቱን እና በስምጥ ሸለቆ ቀጣና በሚገኘው ትልቁ አባያ ኃይቅ ዙሪያ የሚገኝ ስነምህዳርን ለመጠበቅ ዓላማ አድርጐ ነው የተመሰረተው::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ናሽናል ፓርክ አሶሴሽን፣ አውቶሪያ፣ ፊልምፊክሰር እና ጐግል ድረ ገፆችን ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 18  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here