ሚያዚያ 1 ቀን 1966 ዓ/ም በጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓትን ለመመሥረት የታዘዘውን አጥኒ ሸንጎ በማንኛውም ጉዳይ እንደሚተባበረውና እንደሚረዳው አረጋገጠ።
በተጨማሪም መሬትን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ ማንም ሰው ለማልማት ከሚችለው በላይ መሬት መያዝ እንዳይችል እና ወደፊት ከአርሶ አደሮች በስተቀር የእርሻ መሬት ለማንም እንደማይሰጥ ለማድረግ የሚያስችል ሕግ እንደሚወጣ አስታወቀ።