በምሥራቅ ጎጃም መስተዳደር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል በብቸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ቁጥር ብቸ/15/2017
- የጨረታ ዙር 15ኛ
- የጨረታው አይነት መደበኛ ጨረታ
- የመሥሪያ ቤት ስም ብቸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ በማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እና በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው በእለቱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ከጨረታው የመጨረሻ ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ብቸና ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ /ትልቁ አዳራሽ/ ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከተመሰከረለት ባንክ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከአስራ አምስት በመቶ ያላነሰ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ካቀረበው አጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ለመኖሪያና ለንግድ ቦታ ከአስራ አምስት በመቶ ያላነሰ ቅድመ ክፍያ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የዋጋና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላት ኦርጅናል ሲፒኦ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ በአንድ ፖስታ፣ የተሞላውን አንድ ኦርጅናል ሰነድ በአንድ ፖስታ፣ አንድ የተሞላ ኮፒ ሰነድ በአንድ ፖስታ በማሸግና ሦስቱን ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በታሸገው ኢንቨሎፕ ላይ የተጫራቹን ስም፣ የቦታውን ልዩ ኮድ እና የጨረታ ቁጥር በግልጽ በመጻፍ ለቦታው በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ቦታውን ለመጎብኝት ለሚፈልግ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልፀው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ የሚመለስበትን ጊዜ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በ058 665 00 30/ 003/ 10 92 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በብቸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት