የደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማት ማኔጅመንት እና ባንክ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት 02 /ሁለት/ ለድርጅት/ ንግድ 255.6 ካ.ሜ እና 311.42 ካ.ሜ የሚውል ቦታ በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም ሰዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከግንቦት 04/09/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና ለእያዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እናስታወቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከግንቦት 04/09/2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 15/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ቦታዉን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸዉ መርሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ የሚዘጋዉ ግንቦት 15/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ግንቦት 18/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 04፡00 በደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በጋዜጣ እና በአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ዌብ ሳይት እንዲሁም በደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በሳይት ፕላን ላይ በተገለፀዉ እና በከተማዉ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት ደረጃዉን የጠበቀ ግንባታ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 12 47 58 18 /09 31 63 37 72 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት