የካቲት 20 ቀን 1966 ዓ/ም
በኢትዮጵያ የአብዮት ፍንዳታ፣ የወታደሩ
አመጽ ተስፋፍቶ አዲስ አበባ የሚገኙ
የ4ተኛ ክፍለ ጦር፤ የምድር ጦር፤
ዓየር ኃይል እና የዋና መሥሪያ ቤት
ወታደሮች በከተማው ‘ቁልፍ’ ቦታዎችን
በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ። ብዙዎች
የአክሊሉ ሀብተወልድን ሚኒስቴሮች
አገቱ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ
ሥላሴ አቶ እንዳልካቸው መኮንን
ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እና ጀነራል
ዓቢይ አበበን የመከላከያ ሚኒስትር
አድርገው ሾሙ። በወቅቱ አዲስ አበባ
ላይ ሊካሄድ ተዘጋጅቶ የነበረው የአፍሪቃ
አንድነት ድርጅት ስብሰባ በረብሻው
ምክንያት ተሰረዘ።