በአሜሪካ የተወለደው ማልኮልም
ኤክስ ለጥቁር ህዝቦች እኩልነት እና ነጻነት
በቁርጠኝነት ሲታገል ኖሮ ሲታገል ባለበት
የተሰዋ ጥቁር ጀግና ነው። ታዲያ ይህ ጀግና
የተገደለው ዛሬ 59 አመት በፊት ልክ በዚሁ
ሳምንት የካቲት 13 ቀን 1957 ዓ.ም ነበር።
ማልኮልም በእስልምና መንፈሳዊ
አስተማሪ እና ጥቁር አፍሪካዊ አሜሪካውንን
ዘር መድልኦ እና ጭቆናን የሚታገል
ጥቁር ህዝብ መብት ተከራካሪ ነበር።
ማልኮም በህይወት ዘመኑ ለጥቁር ህዝብ
የአሜሪካ መንግስት የሚደርስባቸውን
በደል በአደባባይ ይታገል ነበር። በጊዜው
በየጎዳናው የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችን እና
ተቃውሞዎችን ሲያስተባብር እና ሲመራ
ነበር፤ ማልኮልም ለጥቁር ህዝብ መብት
ሲታገል ስለነበር መንግስት በአድራጎቶቹ
ደስተኛ አልነበረም። በመሆኑም
አለመግባባቱ እያደገ ሄዶ ለሞቱ ምክንያት
እስከመሆን ደረሰ። በዚህ እለትም ነበር
ንግግር እያደረገ ባለበት ባልታወቁ ሰዎች
የተገደለው።