በረንታ ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በምሥራቅ ጐጃም ዞን በሸበል በረንታ ወረዳ ፣ቀበሌ ገዳያሱ ቀበሌ ልዩ ቦታው ጉቢት ቦረቦር ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሸክላ አፈር ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጠው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Adindan UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
No | Easting | Northing |
1 | 436430 | 1159293 |
2 | 436160 | 1159243 |
3 | 435847 | 1159343 |
4 | 435677 | 1159525 |
5 | 435725 | 1159803 |
6 | 435978 | 1159694 |
7 | 436318 | 1159782 |
8 | 436495 | 1159589 |
ብሎክ አንድ
በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
የእርሻ መሬት | የወል መሬት | የእርሻ መሬት | የወል መሬት |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ