የአማራ ክልል ዘር አምራቾች ማህበር የሚጠቀሙበት አርማ /ሎጎ/ እንዲመዘገብ እና ህጋዊ እውቅና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ስለሆነም የአርማውን /ሎጎ/ መመዝገብ የሚቃወም ካለ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት መቃወሚያውን ይዘው በአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የሰነዶች ፣የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶችና የጠበቆች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 እንዲቀርቡ እያሳወቅን እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ ካለቀረቡ አርማውን /ሎጎ/ የምንመዘግብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአብክመ ፍትሕ ቢሮ