ሀሴት በጥራት አነስተኛ ማዕድን ማውጣት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በሰሜን ጎንደር ዞን በምሥ/ ጠለምት ወረዳ ምጫራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሻቁና ተብሎ በሚጠራው ቦታ የወርቅ ማዕድን ምርት ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Adindan UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
Block:-1
| id | X | Y |
| 1 | 437514 | 1517981 |
| 2 | 437517 | 1517899 |
| 3 | 437769 | 1517903 |
| 4 | 437787 | 1517973 |
| በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
| ቃፍታ | ደብረ ጽላ | ማዕከል ምጫራ | 100 ሜትር ርቀት ተከዜ |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ

