ዋይ-ሰርክል /ዩዝ ኳሊዥን ፎር ኢንክሉሲቭ ኮላቦራሽን፣ ሊደርሺፕ ኤንድ ኢምፓዎርመንት የበጎ አድራጎት ማህበራት ህብረት እንዲመዘገብ እና ህብረቱ የሚጠቀምበት ከታች የተቀመጠ (ሎጎ) ህጋዊ እውቅና አዲሰጥላቸው ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም በተላከ ማመልከቻ ጠይቀዋል፡፡ ስለሆነም የህብረቱን ስያሜ እና አርማ (ሎጎ) መመዝገብ የሚቃወም ካለ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት መቃወሚያውን ይዘው አማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የሰነዶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የጠበቆች ጉዳይ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 እንዲቀርቡ እያሳወቅን እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ ካልቀረቡ የቀረበውን ስያሜ እና አርማ (ሎጎ) የምንመዘግብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአብክመ ፍትሕ ቢሮ

