ኤ እና ኤም ኤስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረኤልያስ ወረዳ ገነት ቀበሌ ልዩ ቦታ በለጠች ወንዝ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የግራናይት ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
Adinda UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
No | Easting | Northing |
1 | 313565 | 1124571 |
2 | 313232 | 1124445 |
3 | 313333 | 1124855 |
4 | 312991 | 1124033 |
5 | 313548 | 1124156 |
ብሎክ ቁጥር | በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
1 | ባዶ ቦታ | ዋንጣ የድንጋ ካባ የግራናይት ቦታ | ባዶ ቦታ | ባዶ ቦታ |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ