ያጌት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሰሜን ጎጃም ዞን በባሕርዳር ዙሪያ ወረዳ በኢሳላ ጉላጉልማ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ጥቁር ድንጋይ ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
Adinda UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Gps reading points | ||||
No | Easting | Northing | Area | |
1 | 315420 | 1266253 | 4.09 hectars | |
2 | 315424 | 1266166 | ||
3 | 315515 | 1265965 | ||
4 | 315573 | 1266031 | ||
5 | 315598 | 1266069 | ||
6 | 315636 | 1266118 | ||
7 | 315662 | 1266165 | ||
8 | 315675 | 1266186 | ||
9 | 315681 | 1266197 | ||
10 | 315547 | 1266232 | ||
ብሎክ ቁጥር | በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
1 | ደብረ መድሃኒት ጉላጉልማ መድሃኒዓለም መሬት | ደብረ መድሃኒት ጉላጉልማ መድሃኒዓለም መሬት | ደብረ መድሃኒት ጉላጉልማ መድሃኒዓለም መሬት | ኢሳላ ገብርኤል የ3ቱ ቤ/ክርስቲያን መሬት |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ