እህት መልካሙ አሳየ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ በወምበርማ ወረዳ ፣በጎመር ቀበሌ ፣ ልዩ ቦታ ሶማ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የእምነበረድ ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Adinda UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license are
points | Easting | Northing |
1 | 253761 | 1155022 |
2 | 253526 | 1153912 |
3 | 253684 | 1153948 |
4 | 253978 | 1155022 |
ብሎክ አንድ
በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
ተራራ | ወንዝ | ተራራ | ወንዝ |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ