አኖላ ማውንት ኢንዱስትሪያል ኃ/የተ/የግ/ማህበር በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ዙሪያ ወረዳ በቆጣቦ ቀበሌ ልዩ ቦታ ቦጊር ተብሎ በሚጠራው ቦታ የግራናይት ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
Adinda UTM Zone 37N
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Geographic Coordinates of the license area
| No | X-Easting | Y- Northing | 
| 1 | 286456 | 1144912 | 
| 2 | 286239 | 1144418 | 
| 3 | 286625 | 1144336 | 
| 4 | 286791 | 1144878 | 
| ብሎክ ቁጥር | በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ | 
| 1 | ቦል | የአርሶ አደር ይዞታ | የአርሶ አደር ይዞታ | የማዕድን ቦታ | 
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ


