ምርታማነትን የማሳደግ ተግባራት እየተከናወነ ነው

0
135

በአማራ ክልል በመኸር ወቅቱ የተከናወነው የሰብል ልማት እንቅስቃሴ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ቁመና ላይ እንደሆነ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ሮሜ ቀበሌ በ1 ሺህ 300 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል።
በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ የገለፁት ርዕሰ መስተዳደሩ በመኸር ወቅቱ የተከናወነውን የሰብል ልማት እንቅስቃሴ በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት በሚያግዝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ችግሩን በመቋቋም በመኸር ወቅቱ አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል ማልማት መቻሉን ገልጸዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ ከዚህ ውስጥ ከ870 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ስንዴ በኩታ ገጠም የለማ መሆኑን አመልክተዋል። ቀደም ብሎ 83 ሺህ ሄክታር መሬት የነበረውን የሩዝ ሰብል ልማት ወደ 170 ሺህ ሄክታር መሬት ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል። በአጠቃላይ በመኸር ወቅቱ ከለማው መሬትም 169 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here