በአፍሪካ በስተምእራብ በሲቬልስ ትገኛለች:: ሲሼልስ 115 ደሴቶችን ያቀፈች ሀገር ነች:: በደን በተሸፈኑ ደሴቶቿም ትታወቃለች:: ከቅርብ ዓስርት ዓመታት ወዲህም በቱሪስቶች ተወዳጅ መዳረሻ ሆናለች::
በሲሼልስ ከሚገኙት 115 ደሴቶች መካከልም ሞዬን በሚል ስም የምትታወቀው በስፋቷ ትንሿ ደሴት ተጠቃሽ ነች::
በ1969 አ.አ.አ ብሬንደን ግሪምሾ የተባለ በአቅራቢያው የሚኖር እንግሊዛዊ ደሴቷን ገዝቷታል:: ግሪምሾ ቀደም ብሎ በጋዜጠኝነት ሞያ ነበር የተሰማራው:: ግሪም ሾሞዬንን ከሲሼልስ ተዋውሎ በስምንት ሺህ ፓውንድ ወይም በአሁኑ ምንዛሬ 1,264,240 ብር ነበር የገዛት:: ግሪምሾም በሞዬን በአረም የተተበተቡ ዛፎችን በምንጣሮ የማጽዳት ስራን ሰርቷል- ከሌላው የ19 ዓመት የአካባቢ ተወላጅ ጋር::
በአሁኑ ወቅት ደሴቷ 16 ሺህ ዛፎች ይገኙባታል – አብዛኛዎቹ በግሪምሾ እና አጋሩ የተተከሉ ናቸው:: የተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎችንም አላምደዋል:: ከአካባቢው ተወላጅ አጋሩ ጋር ለዓመታት ያለመታከት በመሥራታቸው የእፅዋት እና የእንስሳት ዝርያዎቹ ተጠብቀው እንዲቆዩ አስችለዋል::
ግሪምሾ ለዓመታት ባደረገው ጥረት ባአቀረባቸው ጥያቄዎች መሰረት ዜሮ ነጥብ አራት 400 ሜትር ርዝመት እና 300 ሜትር ወርድ የተለካው ቀጣና የዓለማችን ትንሿ በሔራዊ ፓርክ ሆኖ እውቅና አግኝቶለታል::
የሲሼልስ አካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴርም የደሴቷ የጥበቃ ሥራ እንዲቀጥል በበላይነት የመቆጣጠር ኃላፊነትን ወስዶ በመስራት ላይ ይገኛል::
በደሴቷ የሚገኝ የእፅዋት ዝርያ ብቻ ሳይሆን በውስጡ ተጠልለው የሚገኙ ለስነምህዳሩ አስፈላጊ የሆኑ የዱር እንስሳት እና ሁለት ሺህ የሚሆኑ ዓእዋፍትም ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው- በተቋሙ::
በደሴቲቱ እፅዋት እና እንስሳትን ለመጐብኘት መንገዶች ተዘጋጅተዋል:: ከውብ የባህር ዳርቻዎች ባሻገር የብሬንደን ግሪምሾ መኖሪያ ቤትም – ታሪካዊ መስህብ ሆኖ ጥበቃ ይደረግለታል:: ለጐብኚዎች ምግብ የሚያቀርብ ሬስቶራንትም ይገኛል:: በደሴቷ ጉብኝት ለማድረግ ቀድሞ ማስታወቅ እና ክፍያ መፈፀም ግድ ይላል:: ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ማይሞደርን ሜት፣ ኤክስኘሎርስ ዌብ፣ ሂስትሪ ሲሸልስ ድረገፆችን ተጠቅመናል::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ዓ.ም ዕትም)