ረሀብ እና ጥም ያልበገረው

0
99

በአሜሪካ ቺካጐ በቅዱስ ካሲሚር ካቶሊካዊ መቃብር ስፍራ ጭንቅላቱ ፈሳሽ መያዣ ከነበረ ኘላስቲክ ውስጥ የተቀረቀረበት አጋዘን በኗሪዎች የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉለትም ከሳምንት በኋላ ራሱን ነፃ ማውጣቱን ዩፑአይ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

ጭንቅላቱ ኘላስቲክ ውስጥ የተጣበቀበትን አጋዘን የተመለከቱ ኗሪዎች ቀርበው ሊያላቅቁለት ጥረት ማድረጋቸውን ያሰነበበው ድረ ገጹ ከእንስሳት መብት ተሟጋቾች ሳይቀር አዘኔታ እንጂ መፍትሄ መስጠት አለመቻሉ ነው ለንባብ የበቃው፡፡

በአቅራቢያው ከከተሙ ኗሪዎች ጄሚ ስታሁላክ የተባለች ቀርባ ኘላስቲኩን ልታወልቅለት ስትሞከር ዘሎ እንዳመለጣት ተናግራለች፡፡ በሌላ በኩል የቀጣናው እንስሳት ጥበቃ ተቋም ባልደረቦችም በድሮን ፍለጋ አድርገው ቢያገኙትም የተጣበቀበትን ለማላቀቅ አለመቻላቸው ነበር ለንባብ የበቃው፡፡

አሳዛኝ እና የብዙዎችን ልብ የነካው ኘላስቲክ ጭንቁላቱ  ላይ የተጣበቀበት  የአጋዘኑ ጉዳይ  የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱንም ድረ ገፆች አስነብበዋል፡፡

በጐ ፈቃደኞች አጋዘኑ ያለበትን ሁኔታ በፎቶግራፍ ቀርፀው በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራታቸው ሃያ የሚሆኑ ኗሪዎች ተሰባስበው እንስሳውን ለመርዳት የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል፡፡

ከፊሎቹ በጐ ፈቃደኞችም ገንዘብ ማዋጣት እና ማሰባሰብ የጀመሩ አንደነበሩ እና በአጋዘኖቹ መኖሪያ ቀጣና በድሮን ቀረፃ እና ክትትል ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡

የበርካቶችን ልብ ያሳዘነው የአጋዘኑ አጣብቂኝ ውስጥ የመግባቱ ሁኔታ መቋጫ ያገኘው ግን በራሱ በአጋዘኑ ቢሆንም ከተጣበቀበት መላቀቁ እፎይታን አስገኝቶላቸዋል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here