ረዥሙ የነፃነት ትግል

0
230

አውሮፓውያኑ የዚያን ዘመን ሃያላን ነን
ባዮች አፍሪካን በቅኝ ግዛት ለመቀራመት
በርሊን ላይ ከህዳር ስድስት እስከ 19/1877
ዓ.ም ጉባኤ ማካሄዳቸውን መነሻ በማድረግ
በተለይም የቅኝ ግዛቱ አተገባበር ደቡብ አፍሪካ
ላይ ምን መልክ እንደነበረው ባለፈው ሳምንት
እትም አስነብቦናል። ቀጣዩ የመጨረሻ ክፍልም
እንደሚከተለው ቀርቧል፤
መልካም ንባብ!
በ1940 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ምርጫ
ተደረገ። በምርጫው የሚሳተፉት ነጭ
ደቡብ አፍሪካውያን እና ክልሶች ብቻ
ነበሩ። አፍሪካውያን የመምረጥ መብት
አልነበራቸውም። ለ38 ዓመታት የደቡብ
አፍሪካ ህብረትን ያስተዳደረው ጄኔራል ኢያን
ስሚዝ በጠባብ ልዩነት ተሸነፈ። የናሽናል ፓርቲ
መሪው ዶ/ር ዳንኤል ማላን አሸነፈ።
ዶ/ር ዳንኤል ማላን ማሸነፉ
ለአፍሪካውያን እና ለእንግሊዝኛ ተናጋሪ
ነጮች(ለእንግሊዛውያን) ጥሩ አልነበረም።
የናሽናሊስቶች ፓርቲ፤ በጥላቻ የተሞላ ፓርቲ
ነው። ለብዙ አስርት ዓመታት የበታች አድርገው
ለገዟቸው እንግሊዞች ጥላቻ ነበራቸው።
የአፍሪካውያን ባህል እንዳያድግ እና እንዲበረዝ
አድርገዋል ብለው የሚያምኑት ናሽናሊስቶች
ለአፍሪካውያን ጥላቻ ነበራቸው። አፍሪካውያኑ
የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ መወሰናቸው
እና በብዙሃኑ አፍሪካውያን የመዋጥ ፍርሀት
ስላደረባቸው በዳንኤል ማላን የሚመራውን
መንግስት ለመምረጥ ተነሳስተዋል። ስለዚህ
የመረጡት መንግስት ሀይል ተጠቅሞ
የበላይነታቸውን እንዲያስጠብቅላቸው
አጥብቀው ይፈልጋሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here