ረጅሙ – ባለክብረወሰን

0
109

በታይላንድ ከተወለደ ሦስት ዓመት ያስቆጠረው ጐሽ ከሸኮናው እስከ ጫንቃው አንድ ሜትር ከሰማኒያ ሴንትሜትር በላይ በተለካ ቁመቱ በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ለክብረወሰን መብቃቱን ኤንዲቲቪ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል::

ከሸኮናው እስከ ጫንቃው ቁመቱ ለሁለት ሜትር ጥቂት ሴንትር ሜትር የቀረው የተለካው በታይላንድ ገጠር ውስጥ ለእርሻ ሥራ የሚያገለግለው ጐሽ በቁመቱ በድንቃድነቅ መዝገብ ለመስፈር በቅቷል::

በታይላንድ ናኮን ራቻሲማ ውስጥ ኒላኔ መንደር በእርሻ በሚተዳደሩ ሲካርት ቦንቻሮን የተሰኙ አሳዳሪው ቤት ሚያዚያ 1/2021 እ.አ.አ መወለዱን ለክብወረሰን መዝጋቢ ባለሙያዎች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል- ባለንብረቱ እና ጐረቤቶች::

ግዙፉ እንስሳ በተፈጥሮው የማይተናኮል ወይም አስቸጋሪ አለመሆኑን፣ በቀጣናው ባለ ኩሬ ውስጥ መንቦጫረቅ የሚያዘወትር፣ ከሚንከባከቡት ሰዎች ጋር መቀራረብ  እና መተሻሸት የሚሻ መሆኑን ነው የጠቆሙት- አሳዳሪው::

ጐሹ ከተወለደ ጀምሮ ቁመቱ ከፍ ያለ በመሆኑ  “ኪንግ ኮንግ” በተሰኘው ፊልም ላይ ባለው ግዙፉ የጐሬላ ስም “ኪንግ ኮንግ” ተብሎ መጠራቱን አስረድተዋል-አሳዳሪ ባለቤቱ::

ግዙፉ ጐሽ በሚኖርበት የእርሻ ቦታ የሚሰሩት ቼርፓት ዉቲ የተባሉት ግለሰብ ለክብረወሰን መዘጋቢዎች ከሌሎች በአካባቢው ከሚገኙ ጐሾች ከውልደት ቀኑ ጀምሮ በቁመት ዘለግ ያለ  ብልጫ እንደ ነበረው ነው የተናገሩት:: ከተወለደ ገና ሦስት ዓመቱ በመሆኑም ከዚህ የበለጠ ቁመቱ እንደሚጨምር እምነታቸው  ስለመሆኑ መናገራቸውን ድረ ገጹ አስነብቧል::

በአካሉ ግዝፈት ሲያዩት አስፈሪ ቢመስልም ከሰዎች ጋር መቀራረብን የሚሻ፣ ለማዳ፣ ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር ታዛዥ መሆኑንም ነው ያሰመሩበት – ቼርፓት ዉቲ::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 17  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here