ሰብል ለማጓጓዝ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
134

በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬንኃ.የተ. 40,000 /አርባ ሺህ ኩ/ል/ ከዳሞት ዩኒየን መጋዝን ወደ ወረታ አዳጋ ስጋት መጋዝን ግልፅ ጨረታ በማውጣት ማጓጓዣ ይፈልጋል:: ስለሆነም፡- ተጫራቾች ደረጃ አራት አጓጓዥ ድርጅት መሆን አለበት::

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ::
  2. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋው ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ወይም ማስያዝ አለባቸው::
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 00 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ::
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 11 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል:: ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጎልም::
  6. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት ተወካይ ከሆኑ የውክልና ወረቀት አብረው ያያይዙ::
  7. አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሁለት በመቶ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል::
  8. ተጫራቹ በራሱ ስም የተዘጋጅ የማጓጓዣ ሰነድ /ዲስፓች/ ማዘጋጀት አለበት::
  9. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  10. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል::
  11. የማጓጓዣ ጊዜ (አጓጉዘው የሚጨርሱበት ጊዜ) ውል በሚይዙበት ሰዓት ይገለጻል::
  12. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /1032 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ::
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬንኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here