ሲመተ ልጅ እያሱ

0
285

ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም ዓፄ ምኒልክ በህመም ባሉበት ወቅት ቀጣዩ የሀገሪቱ ንጉሥ ማን እንደሚሆን ሁሉም በተጨነቀበት ወቅት ነበር ልክ በያዝነው ሳምንት በግንቦት 10 ቀን 1901ዓ.ም ላይ ነበር ቀጣዩ ንጉሥ የታወቀው።
ዐፄ ምኒልክ ከአልጋ ለአፍታ ተነስተው ቀጣዩ አልጋ ወራሽ የልጅ ልጃቸው ልጅ እያሱ መሆኑን የኃይማኖት መሪዎች እና ሹማምንቶቻቸው ባሉበት አወጁ። በንግግራቸውም፣ “…አሁንም እንደተመኘሁት እግዚአብሔር የተጨመረበት እና ፈቃዱ ሆኖ ልጄን ቢያቆምላችሁ ከልጄ ጋር ሆናችሁ ሀገራችሁን ጠብቁ አደራ ብያችኋለሁ” ብለው ነበር።
ምንጭ- ባሕሩ ዘውዴ የኢትዮጵያ ታሪክ 1847 እስከ 1983

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here