ሲንኬ ቴሬ ብሔራዊ ፓርክ

0
121

ሲንኬ ቴሬ ብሔራዊ ፓርክ በጣሊያን ሰሜናዊ ክልል በሊጉሪያ አውራጃ ነው የሚገኘው:: ጠቅላላ ስፋቱም 38 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል:: በአገሪቱ ከሚገኙ በስፋት ትንሹ ፓርክ ነው::

ሲንኬ ቴሬ ብሔራዊ ፓርክ በሊጉሪያ የባህር ዳርቻ ባለ ድንጋያማ ኮረብታ ወይም አግድም በተዘረጋ ገደል ጐን ላይ የከተሙ አምስት መንደሮችን ያቀፈ ነው:: መንደሮችም ኮርኒግሊያ፣ ማናሮላ፣ ሞንቴሮሶ ኦልማሬ፣ ሪዮማጆሬ እና ቬርናዛ ይሰኛሉ:: በአምስቱ መንደሮችም አምስት ሺህ ኗሪዎች ይገኛሉ::

ሲንኬቴሬ ብሔራዊ ፓርክ በ1999 እ.አ.አ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን በባህሩ ዳረቻ ባለው ገደለማ ኮረብታ በተቆረቆሩት መንደሮች የሚገኙት ኗሪዎች ለቀጣናው ተፈጥሯዊ ሀብት ጥበቃ የሚያደርጉት አስተዋፆኦ ከፍተኛ መሆኑን በግልፅ የሚያመላክት ነው:: ኗሪዎቹ ለተፈጥሯዊው ስነ ምህዳር፤ ስነምህዳሩም ለኗሪዎቹ ህልውና አንዱ ለአንዱ የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑ ነው በድረ ገፆች የተብራራው ::

አምስቱ በባሕር ዳርቻ በሚገኘው ገደላማ ጉብታ ላይ የከተሙት መንደሮች አንዱ ከአንዱ የሚያገናቸው የእግር መንገድም አላቸው:: በቀጣናው ከእፅዋት- ጥድ፣ የተለያዩ ቁጥቋጦዎች በየገደሉ ዳርቻ ይታያሉ::

ከዱር እንስሳት ቀበሮ፣ የዱር አሳማ፤ ከዓእዋፍት የባህር ጭላት (ሲገል)፣ “ኘሪግሪን ፋልኮን” መገኘታቸው ተረጋግጧል::

ሲንኬ ቴሬ ብሔራዊ ፓርክ በልዩ ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊ መስህብ መገኛነቱ በዓመት አምስት ሚሊዬን ሰዎች እንደሚጐበኙትም ነው የተጠቆመው::

በባህሩ ዳር በሚገኘው አቀበት ላይ በከተሙት መንደሮች ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻ አምስተኛው በእግር መጓዝ ለጐብኚዎች የደስታ፣ ለኗሪዎቹ የገቢ ምንጭ መሆኑም ነው የተገለፀው:: ጐብኚዎች በአምስቱ መንደሮች በእግር ሲጓጓዙ ከፍ ካለው ጉብታ ቁልቁል የባህሩ ዳርቻ የሚቃኙበት ሁነት አይረሴ መሆኑንም አብኛዎቹ ከሰጡት አስተያየት አብነት ሆኖ ለንባብ በቅቷል::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ናሽናል ፓርክ ዶት ኦርግ፣ ኢታሊቱር ኢንኔቸር እንዲሁም ሲንኬቴሬ::፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here