ሻላ ሐይቅ

0
104

የሻላ ሐይቅ በጥልቀት እንዲሁም በውኃ ይዘት መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሐይቆች መካከል የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል።

ሐይቁ በዋናው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ይካለላል። ከባህር ወለል በላይ አንድ ሺህ 559 ሜትር ከፍታ አለው። ከአዲስ አበባ በስተደቡብ፣ በሞያሌ መንገድ 225 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

የሐይቁ ርዝመት 27 ኪሎሜትር፣ አጠቃላይ ስፋቱ ደግሞ 314 ኪሎሜትር ስኩዌር ነው። የሻላ ሐይቅ ጥልቀት226 ሜትር ሲሆን በተደጋጋሚ የሚከሰተው ጥልቀት ደግሞ 86 ሜትር ነው።

ሐይቁ የሚይዘው የውሃ መጠን 38 ቢሊዮን ሜትር ኩብ እንደሆነ ይገመታል። ይህ የውሃ መጠን በሌሎቹ የኢትዮጵያ ሐይቆች ማለትም ጣና፣ ዝዋይ፣ አብያታ፣ ላንጋኖ እና የአዋሳ ሐይቆች በአንድ ላይ ሆነው ከሚይዙት የውሃ መጠን እጅግ የላቀ ነው።

ምንጭ፦ www.wikimapia.org

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 24  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here