በአማራ ክልል የተፈጠረው
በትጥቅ የታገዘ ግጭት እልባት
እንዲሰጠው ብዙዎች እየጠየቁ
ነው። ሰላም እንዲሆን ሁሉም
ይፈልጋል። ነገር ግን ሰላም
የሚመጣበት መንገድ ላይ
ተመሳሳይ አቋም ያለ
አይመስልም።
በአዲስአበባ ዮኒቨርሲቲ
የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት
ዶክተር ዳር እስከዳር ታዬ
ለበኩር እንደተናገሩት የሰላም
ድርድር ወይም ንግግር ሁሉንም
ለአሸናፊነት የሚያበቃ ሀይል
ነው። ግጭቶችን ለማርገብ፣
ቀውሱን ለመቀልበስ እና ወደ
ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ
ሀቀኛ ንግግሮች ገቢራዊ ሊሆኑ
እንደሚገባ የጠቆሙት ምሁሩ
በሰጥቶ መቀበል መርህ ጫፍ
ላይ ሳይሆኑ ወደ መሃሉ
በመቅረብ ለሰላም መሥራት
እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የተለያዩ
የፖለቲካ ፓርቲዎች ንግግር
እንዲደረግ የመሣሪያ አፈሙዞች
እንዲስተካከሉ እየወተወቱ
ይገኛሉ። ለፖለቲካዊ ችግሮች
ፖለቲካዊ ምላሽ ማዘጋጀት
እንጅ ውጊያን አማራጭ ማድረግ
አውዳሚ መሆኑን ከታሪክ
ሳይሆን አሁን እየሆነ ካለው
መማር ይቻላል።