ቀዳሚዉ የዕድሜ ባለፀጋ

0
151

በእንግሊዝ ሊቨርፑል የተወለደው የዓለማችን የ111 ዓመቱ ጆን አልፍሬድ ቲኒስውድ በአለፈው መጋቢት ወር ጃፓናዊው የዓለማችን የዕድሜ ባለፀጋ ጂስቡሮ ሳኖቢ በ112 ዓመቱ በመሞቱ የረዥም ዕድሜ ባለፀጋነት ክብረወሰንን በተተኪነት መያዙን ዘጋርዲያን ድረገጽ አስነብቧል፡፡

ጆን አልፍሬድ ቲኒስውድ የተወለደው ታሪካዊዋ ታይታኒክ መርከብ በሰጠመችበት ዓመት በ1912 እ.አ.አ ነበር፡፡ ጆን አልፍሬድ ባለፈው መጋቢት ወር መጨረሻ የ112 ዓመቱ ጃፓናዊ ጂስቡሮ ሶኖቤ ሕይወቱ ማለፉ ከተረጋገጠ በኋላ የዓለማችን በእድሜ አንጋፋው ሰው የመሆን ማዕረግን ተቀዳጅቷል፤ በዓለም የክብረ ወሰን መዝጋቢው ድርጅት፡፡

ጆን አልፍሬድ  ቲንስውድ ቅድመ ዓያት ለመሆን በቅቷል፡፡ በሊቨርፑል ከተማ የተወለደው የዕድሜ ባለፀጋ በዕድሜ አንድ መቶ ዓመት ከአስቆጠረበት 2012 እ.አ.አ ጀምሮ ከንግስት ኤልሳቤት የእንኳን አደረሰህ የልደት ካርድ ሲላክለት እንደነበር ነው የተናገረው፡፡

ሰው ያለውን እንዲሰጥ እና መጨነቅ እንደሌለበት የሚመክረው ጆን አልፍሬድ “ከሌሎች ለመማርም ሆነ ሌሎችን ለማስተማር የምትችለውን ሁሉ አድርግ” ሲል ነው በአጽንኦት ያሰመረበት፡፡

አመጋገቡን በተመለከተ የዕድሜ ባለፀጋው እንክብካቤ የሚያደረጉለት የሚሰጡትን ከመብላት ውጪ የተለየ ልምድ እንደሌለው ነው የተናገረው፡፡

በየዕለቱ የሚያከናወናቸውን ተግባራት ያለምንም ረዳት በራሱ እንደሚፈጽማቸውም ነው ለሌሎች ተሞክሮውን ያጋራው፡፡ ዘወትር ጠዋት ተነስቶ  ቁርሱን ይበላል ከዚያም የራዲዮ ዜና ያዳምጣል፡፡

ጆን አልፎ ሬድ ቲኒስውድ በሁለቱም የዓለም ጦርነቶች በአካል ነበር፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ግን በወታደርነት ተሣትፏል፡፡

በጦርነቱ ከተካፈሉ እና በሕይወት ካሉ የዕድሜ ባለፀጋዎች አንዱ ለመሆንም በቅቷል፡፡

የዕድሜ ባለፀጋው በሊቨርፑል ዳንስ ላይ ተዋውቀው ያገባት ባለቤቱ በ1986 እ.አ.አ ከመሞቷ በፊት ለ44 ዓመታት አብረው ኖረዋል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here