በሰሜን ወሎ ዞን በአንጎት ወረዳ የአሁንተገኝ ጤና ጣቢያ

0
265

የጨረታ ቁጥር 01/2016

በሰሜን ወሎ ዞን በአንጎት ወረዳ የአሁንተገኝ ጤና ጣቢያ በ2016 ዓ.ም በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት ሎት 1. የቢሮ እቃ፣ ሎት 2. ህትመት፣ ሎት 3. ኤሎክትሮኒክስ፣ ሎት 4. የጽዳት እቃ ሎት 5.
ደንብ ልብስ ቴትረን፣ ሎት 6. ሸሚዝ፣ ሎት 7. ጫማ እና ሎት 8. ስፌት ኮትና ጉርድ ቀሚስ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
1. በየዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ምዝገባ፣ /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ግዥው ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል አሁንተገኝ ጤና ጣቢያ የግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት ዕቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ከአሸነፈበት ሃያ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/
በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ በመቁረጥ ፖስታው ውሰጥ አሽጎ /አያይዞ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ የሞሉበትን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አሁንተገኝ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ተጫራቾች /ሕጋዊ/ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሁንተገኝ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 4 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
8. የአሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ አስር በመቶ በማቅረብ ዕቃዎችን አሁንተገኝ ጤና ጣቢያ ለማስረከብ
ውለታ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
9. የጨረታ መክፈቻ የመጨረሻ ቀን ዝግ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
10.ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ በጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 45 70 98 89 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
11.ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተጫራቾች መመሪያ ተያይዟል፡፡
12.መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

የአሁንተገኝ ጤና ጣቢያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here