በስፋቱ አንደኛነትን የተረከበዉ

0
135

በህንድ ጉጅራት ግዛት አዲስ የተከፈተው የአልማዝ ማእድን መቆራረጫ እና የሽያጭ ማእከል በግዝፈት ቀዳሚ ደረጃ መያዙ ተዘገበ፡፡

በ35 ሄክታር መሬት ላይ መሀል ለመሀል በጋራ መተላለፊያ ግድግዳ የተገናኙ ዘጠኝ ባለ 15 ፎቅ ህንፃዎችን የያዘው ይኸው ማእከል በስፋቱ ወይም በግዙፍነቱ ቀዳሚ  ሆኗል ነው ያለው  ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ፡፡

ላለፉት 80 ዓመታት በ66 ሚሊዬን 73 ሺህ ስኩዬር ጫማ ስፋት የዓለማችን ትልቅ ወይም ግዙፍ ህንፃ ማእረግ በአሜሪካዉ የ“ፔንታጎን”  ህንፃ የተያዘ ነበር፡፡ በቅርቡ ግን  አዲስ በተገነባው የዓልማዝ ማእድን የንግድ ማእከል በ55 ሺህ ስኬዌር ጫማ ተበልጦ የአንደኛነቱን መንበር አስረክቧል፡፡

በህንድ ሱራት ዳርቻ  ላይ የተገነባው ይኸው ህንፃ ከ4700 በላይ የጽህፈት ቤት እና የእደ ጥበብ ባለሙያ የስራ ክፍሎች  ያሉት ሲሆን 131 አሳንሰሮችም ተገጥመውለታል፡፡

ከዓለማችን 90 በመቶ የሚሆነው የዓልማዝ ጌጣጌጥ ግዥ እና ሽያጭ በዚሁ ማእከል እንዲከወን የእደ ጥበብ ባለሙያዎችን እና ነጋዴዎችን በአንድ ጣሪያ ስር ማሰባሰብ እንጂ ክብረ ወሰን መስበር ግባቸው እንዳልነበር የጠቆሙት ንድፉን የሰራው ድርጅት መስራች በመጨረሻ በድል መጠናቀቁንም ነው ያበሰሩት፡፡

ዘጠኝ በአራት መእዘን ቅርፅ የተገነቡ ባለ 15 ፎቅ ህንፃዎች ግራ እና ቀኝ በሚከፍላቸው የጋራ ግድግዳ ለሚገናኙበት ግዙፉ የንግድ ማእከል ግንባታ 32 ቢሊዮን “ሩፒ” የህንድ ገንዘብ ወይም 388 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ግዙፉ ህንፃ 65 ሺህ ሰዎችን፣ 4,500  ባለ አራት ጐማ እንዲሁም 10 ሺህ ባለ ሁለት ጐማ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ እንደሚችልም ተጠቅሷል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here