በአራት እጥፍ የጨመረዉ

0
53

“የዓለማችን በልጦ ማቀዝቀዣ” በመባል የሚታወቀው የአርክቲክ ወይም ሰሜን ዋልታ ከቅሪት አካል  ከሚገኘው ነዳጅ የሚወጣው በካይ ጢስ ልቀት ምክንያት ከዓለም አቀፍ አማካይ አራት እጥፉ በልጦ እየሞቀ መሆኑን  ዘጋርድያን ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት አስነብቧል::

ከጥቅምት ወር 2024 እስከ መስከረም 2025 እ.አ.አ አብዛኛው የአርክቲክ ክልል የሙቀት መጠን ባለፉት 125 ዓመታት ከተመዘገበው በእጅጉ የጨመረ መሆኑን የአሜሪካ ብሔራዊ ውቅያኖስ እና የአከባቢ ዓየር አስተዳደር (Noaa) አስታውቋል::

ቀሪው የዓለማችንን ክፍል ከሙቀት የሚከላከለውን  የአርክቲክ ቀጣና ከቅሪት አካል ከሚገኘው ነዳጅ የሚወጣው በካይ ልቀት ከባቢ ዓየሩን ያዛባዋል። ይህም በክልሉ የሚኖሩ እንስሳት እና እፅዋት ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉ ነው የተብራራው -በድረ ገጹ::

ሁነቱን የሚከታተሉ ተመራማሪዎች እንዳሉት  ባለፉት 47 ዓመታት የበረዶው መጠን በእጅጉ እየቀነሰ  ነው።

በአሜሪካ የኮሎራዶ ዩኒቨርሲቲ የአርክቲክ ቀጣና ከፍተኛ ተመራማሪ ማቲው ላንግደን ከ2024 እስከ 2025 እ.አ.አ ያለው ዓመት የመጪዎቹን ዓመታት አስከፊነት አጉልቶ ያሳየ መሆኑን ነው ያሰመሩበት:: ለዚህም በበረዶ ግግሮች መጠን መቀነስ፣ የዋልታ ድብን የመሰሉ የቀጣናው የዱር እንስሳት ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁን አብነት አድርገው  አንስተዋል::

ተመራማሪዎቹ  እንዳሳሰቡት ባለፈው ዓመት የነበረው የግግር በረዶ መጠኑ በያዝነው ዓመት በእጅጉ ቀንሷል:: የበረዶ ብናኝ መውረዱ ቀርቶ ኃይለኛ ዝናብ ተስተውሏል:: በዚህም ግግር በረዶው እየቀለጠ ከስር የነበረው አፈር እየተሸረሸረ ወደ ውቅያኖስ እየገባ ነው::

በመጪዎቹ ዓመታትም የባህር ወለል መጠን በእጅጉ ጨምሮ በዙሪያው በሚገኝ የየብስ ቀጣና የሰፈሩ  ኗሪዎችን ያፈናቅላል ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የታህሣስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here