በእድሜው ክብረወሰን ያገኘዉ

0
20

በቲቤት ምሥራቃዊ ግዛት በዱርውስጥ የተገኘው የወይን ተክል 416 ዓመታትን ማስቆጠሩ በመረጋገጡ በዓለም አቀፉ የድንቃ ድንድ መዝጋቢ ድርጅት ጥንታዊ የወይን ተክል በሚል ለክብረወሰን መብቃቱን ኦዲቲ ሴትንራል ድረ ገጽ ከሳምንት በፊት ለንባብ አብቅቶታል፡፡

“ማቱሳላው” የዋይን ተክል በቲቤት ዞንግ ግዛት ዙአባ በተሰኘ መንደር ነው በባለሙያዎች የተገኘው፡፡

በቀጣናው የመስክ አሰሳ ሲያደርጉ የነበሩ የቻይና ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች እድሜ ጠገቡን ተክል  ማግኘት ችለዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ  ባደረጉት የግንዱ የቀለበት ቆጠራ ግምት እና የላቦራቶሪ ምርመራ  ውጤት 406 ዓመታት መቆየቱንም አረጋግጠዋል፡፡

የወይን ተክሉ ከበቀለበት መሬት ስምንት ሜትር ቁመት፣ የታችኛው የግንዱ ውፍረት ዙሪያ ልኬት ደግሞ 209 ሴንት ሜትር ተለክቷል፤ ይህም የተለየ ባለክብረወሰን  አድረጐታል፡፡

በበርካታ አገራት በአበዛኛው ከ50 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ የወይን ተክል አለመኖሩን ያስነበበው የድረ ገጹ ጽሁፍ በዞንግ ግዛት ግን ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ ከ64 በላይ የወይን ተክሎች  መኖራቸውን በመስክ ምልክታቸው አረጋግጠዋል- ተመራማሪዎቹ፡፡

በግዛቷ ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ የወይን ተክሎች ለመገኘታቸው ተመራማሪዎቹ ምክንያቱን ለማወቅ ጥረት አድርገዋል፡፡ ለዚህ መሰረቱ በቀጣናው የወይን ጠመቃ ከ1000 ዓመታት በላይ የዘለቀ ታሪክ ያለው መሆኑን በአስርጂነት መገንዘብ ችለዋል፡፡

በመጨረሻም በቲቤት እስከ 2400 ሜትር ከፍታ ባለው ተራራማ ቀጣና ወፍ ዘራሽ እድሜ ጠገብ የወይን ተክል መገኘቱ አስደናቂ መሆኑን በመጥቀስ ነው የድረ ገጹ ጽሁፍ ያደማደመው፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here