በደን የተከበበው ‘ኬሬላ’

0
51

በህንድ ትሪሱር አውሪጃ፣ ቫንዳራፒሊ ቀጣና በጥቅጥቅ ደን መካከል የሚገኝ የ “ክሪኬት” መጫዎቻ ሜዳ በማህበራዊ ድረ ገፆች ምስሉ ለእይታ በቅቷል፤ በሳቢ እና ማራኪነቱም በሚሊዮኖች መደነቁን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል።

የክሪኬት ሜዳውን ከበርካታ ዓመታት በፊት በቀጣናው በእርሻ ስራ የተሰማራ ሃሪሰን ማላያላማ የተሰኘ ኩባንያ ለሰራተኞቹ በመዝናኛ ቦታነት ነበር ያዘጋጀው፡፡

 

ድረ ገጹ እንዳሰፈረው ኩባንያው ስራውን ጨርሶ ሲለቅ ለአካባቢው ኗሪ አገልግሎት መስጠቱን ቀጥሏል- በደን የተሸፈነው ሜዳ፡፡

የክሪኬት ሜዳው በማህበራዊ ድረ ገጽ ለእይታ እንደበቃ 38 ሚሊዬን እይታ (view) እና አራት ነጥብ አምስት ሚሊዬን መጋራት (ሼር) መደጉን ድረ ገጹ አስነብቧል። በነባር ነዋሪዎችዋ የ“እግዚአብሄር አገር” ተብላ በምትጠራው ኬሬላ ከተፈጥሯዊ ውብቷ ባለፈ ተጨማሪ ጌጥ እንደሆነላት አስተያየት ሰጪዎች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

 

በርካታ በማህበራዊ ሚዲያ የሜዳውን እና የከበበውን ለምለም ደን የተመለከቱ፤ ማመን ተስኗቸው በሰውሰራሽ ኪሂሎት (AI) የተቀናበረ ነው የሚል አስተያየት መሰንዘራቸውን ነው ድረ ገጹ ያስነበበው፡፡

 

የስፓርት ጨዋታው በእጅጉ ተወዳጅ ሆኖ በሚዘወተርባት ህንድ ከበርካታ ዓመታት በፊት የተሰራው እና ዛሬም ሳቢ እና ማራኪነቱን እንደያዘ የዘለቀው የክሪኬት ሜዳ በደን መመንጠር ለከፋ ችግር ተጋላጭ እየሆነ መጥቷል።

በደን ወደ ተከበበበው ሜዳ ለመግባትም ሆነ ለመውጣት ያለው አንድ ቀጭን መተላለፊያ መንገድ ብቻ መሆኑን ያስነበበው ድረ ገጹ ሜዳው በሁሉም መመዘኛ ተመራጭ እና ሳቢ ነው፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here