የአብክመ ጤና ቢሮ የሚጠቀምባቸውን የስራ ክፍሎች አመታዊ ውል በመያዝ ለማፀዳት በዘርፉ ለተሰማሩ አውት ሶርስ በማድረግ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርቡ፡፡
- ከላይ በተራ. ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ በጤና ቢሮ በግዥ ፋይ/ ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ16ኛው ቀን 8:30 ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን የፅዳት ቁሳቁስ እና የቢሮ ፅዳት አገልግሎት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አግባብ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ከነሐሴ 26/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮው የሰነድ ሽያጭ ክፍል መውሰድ ይችላል ፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታዉ መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር 058-222-11 27 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የአብክመ ጤና ቢሮ