በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
78

በሰሜን ወሎ ዞን የወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት የሰርቨር እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር እቃ ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች በሙሉ፡-

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላችሁ፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
  4. የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ የሆነ፡፡
  5. ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማንኛውም ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጀቱ ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል ፣ተጫራቾች ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡ በቀረቡት እቃዎች ላይ ችግር ቢፈጠር የመመለስ /የመቀየር/ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በህግ ፊት ይጠየቃሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ድምሩ ከ10,000 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ሁለት በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. የአሸነፉበት የእቃ ድምር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት እቃዎች እስከ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  11. ተጫራቾች የሞሉት እቃ ድምር ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዘው መቅረብ አይፈቀድም፡፡
  12. የጨረታ ሰነዱን በወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ሰነድ በብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  13. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡
  14. የሚገዙት እቃዎችን  ዝርዝር ከመ/ቤቱ ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች ለአማራ ክልል ከተሞች የመጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ እና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1/2004 ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  16. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት በ16 ተኛው ቀን  የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ይሆናል፡፡
  17. ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04  ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  18. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  20. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በውሃ አገልግሎቱ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 003 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ፣Email gechmog@gimail.com ፣ፋክስ 033 331 15 72 በስልክ ቁጥር 033 431 07 99 /033 431 12 23 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የወልድያ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here