የጨረታ ቁጥር 02/2017
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት የሚያስፈልጉ ሎት 1. የሰራተኞች የደንብ ልብስ /ብትን ጨርቆች/፣ የተዘጋጁ ሸሚዞች፣ የወንድና የሴት ቆዳ ጫማ፣ የወንድ የፕላስቲክ ቦት ጫማ እና ልዩ ልዩ አልባሳት ፣ ሎት 2. የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ሎት3. ቱልስ ፣ ሎት 4. ቧንቧና መገጣጠሚያ፣ ሎት 5. ፓምፕና ጀኔሬተር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎች የተመዘገቡ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ለሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን የዕቃዎች የጠቀሜታ ዝርዝር መግለጫ ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ናሙና ወይም ለሚያስፈልጋቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ / በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ዘውትር በስራ ሰአት ቢሮ.ቁ 03 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል በማለት ህጋዊ መረጃዎችን ከቴክኒካል ፖስታ ውስጥ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሸያን መረጃዎቻቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በፋይናንሽያል ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ከጧቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በአስራ አምስተኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 01 በይፋ ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የዕረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዱ እስከ 4፡00 ድረስ በማስገባት ከቀኑ 4፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት 100MM 0.30510272
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት