መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ ጤፍ የአንዳቤት እና የእስቴ ምርት የሆነ 1200 ኩንታል ነጭ የበዛበት ሰርገኛ ጤፍ እና 600 ኩ/ል በቆሎ በድምሩ 1800 ኩ/ል ሰብል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዚህ ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይምበጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ተጫራቶች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን እና ተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሃምሳ) ብር መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል በመግዛት የመወዳደሪ ዋጋ፣ስማቸውን፣ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተዘረዘሩትን ሰነዱን በመግዛት ዋጋቸውን ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታዎቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተሸጦ በ10ኛው ቀን 8፡00 ሰአት ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡10 ሰአት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 10ኛው የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል ፡፡
- የማስረከቢያ ቦታ ዩኒዬኑ መጋዘን ደብረ ታቦር ላይ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ጨረታ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ናሙናውን ማየት እና በናሙናው መሰረት መሆኑን ከመጫኑ በፊት ከቦታው የዩኒዬኑ ባለሙያ ሲያረጋግጥ ብቻ የሚጫን ሲሆን በ10 ቀን ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ የሞላው ሲሆን አሸናፊው በተለይ በ5ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪያ የዋጋውን 10በመቶ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅበታል ፡፡
- ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0584411336 /0581412864 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መገናኛ ሁለ /የገ/ህ/ስ/ ማህበራት ዩኒዬን