ቁጥር 3
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉሉ ያገለገሉ ዕቃዎችን 1ኛ. ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ 2ኛ. ያገለገሉ የተለያዩ ፈርኒቸር ዕቃዎችን በድጋሜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 ሰነዱን በመዉሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ም/ዳይሬክተር ቢሮ 1ኛ. ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፤ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- ለጨረታው ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን ሲሆን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚሸጡ ዕቃዎች ዓይነትና ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋናው ቢሮ ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ከገጠር መንገድ ቢሮ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን