በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 በጀት አመት ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች አገልግሎት የሚዉል የመኪና የጭነት ኪራይ ባሕር ዳር ደርሶ መልስ ኦክስጅን ሲሊንደር አስሞልቶ ጭኖ ለማምጣት እና መድህኒት ከጎንደር ወደ መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማስመጣት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር የከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- (የቫት) ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመኪናውን ሊብሬ ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ፎቶ ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ለጨረታ የሚቀርበው ተሸከርካሪ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት ሚውል መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፡፡
- ኦክስጅን ሲሊንደር ያልተሞላውን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ጭኖ ባሕር ዳር ኦክስጅን ማምረቻ አስሞልቶ መተማ ሆስፒታል ማምጣት የሚችሉ፡፡
- የመድን ኢንሹራንስ ውል ያላቸው እና ኮፒውን ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በመተማ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን ከነሐሴ 19/2017 እስከ ዻጉሜ 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ዻጉሜ 4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለው እና ሰነዱ ላይ ሥም እና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 01 74 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጭነት ዋጋ አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጭነቱ አይነት በቢያጆ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ እንዲጫን በሚጠየቅበት ሰዓት በአስቸኳይ ማምጣት የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ኦክስጅን ሲሊንደር ከመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ባሕር ዳር ጭኖ አስሞልቶ ለማምጣት በሚሄድበት ቀን በመብራት መጥፋት ምክንያት ወይም በወረፋ ምክኒያት ቢዘገይ ወረፋውን ጠብቆ አስሞልቶ መምጣት የሚችል፡፡
የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል