የባህርዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል ሎት1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ሎት 2. ብረታብረት ፣ሎት3. የመኪና ዘይት እና ቅባቶች፣ ሎት4.የብስክሌት መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት /ቲን/ ያላቸዉ ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋዉን ጠቅላላ አንድ በመቶ ሲፒኦ ወይም በገቢ ደረሰኝ መሂ1 ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡
- ዋጋቸዉ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ /ብር በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ማዕከሉ ከሚገዛዉ ዕቃ የዋጋዉን 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለዉ፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት የዉል ማስረከቢያ የዉሉን ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ዋጋ በመሆኑ ሁሉንም የተዘረዘሩት ዕቃዎች መሙላት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 70.00/ ሰባ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ ፡፡
- የእቃዎችን አይነት /ሞዴል /ማዕከሉ ድረስ በአካል መጥቶ ማየት ይቻላል፡፡
- ጨረታዉ በአየር ላይ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል ፤ ቀኑ ቅዳሜ ፣እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ ከማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ለወደፊትም ከመንግስት ግዥ እንደማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
- ማዕከሉ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተጫራቶች በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በተዘረዘረው ጥራት መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-321-54-82/058-820-97-84 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባህርዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል