በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
74

የግዥ መለያ ቁጥር አ/ማ/ግ/05/2017
በአብክመ የሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ለተጎዱ የመንግስት ተቋማት እና ለዲጅታል አይዜሽን አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ማለትም እንደ ሰርቨር፣ ኮምፒተር ፣ፕሪንተር ፣እስካነር እና የመሳሰሉትን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
3. የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛዉ ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ቴክኒካል ግምገማ ለሚያስፈልጋቸዉ ዕቃዎች የመጫረጫቻ ሰነዱን በትክክል ከሞሉ በኋላ ቴክኒካሉን እና ፋይናሻሉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች ቴክነካል ግምገማ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች የመጫረቻ ሰነዱን በትክክል ከሞሉ በኃላ ቴክኒካሉን እና ፋይናሻሉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582220580 በመላክ ወይም በስልክ 0582209644 /0582209646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here