የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለማኒፋክቸሪንግ ፣ለኤሌክትሪክሲቲ እና ለኮንስትራክሽን የግንባታ ጥሬ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 100,000/ መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታው ዉድድር በነጠላ ድምር ዋጋ ሆኖ አሸናፊ እና ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ በባለሙያዎች እየተረጋገጠ ዕቃዎችን ገቢ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የለባቸውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር 10,000/አስር ሽህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ማለትም ዋናና ቅጅ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ወይም ገጽ ላይ የድርጅቶች ማህተም በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋ/ን/አስ/ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከ2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከ 6 /08/2017 ዓ.ም እስከ 20/08/2017ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 2፡30-11፡00 እንዲሁም በ21/08/2017 ዓ.ም እሰከ ጥዋቱ 3፡00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋ/ን/አስ/ ቡድን ክፍል 21/08/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡05 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ሲሆን ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ቁጥር 0581118360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ