በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የመገናኛ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ. በሎት /በምድብ/:- ሎት1. ስኳር ማጓጓዝ በየዙሩ 1101 ኩ/ል ከመትሃራ ወይም ወንጅ ወይም አዲስ አበባ ወደ ደ/ታቦር እና ወረታ ከተማ፣ ሎት2. የምግብ ዘይት ማጓጓዝ በየዙሩ 134 ሽ ሊትር ከአዲስ አበባ ወደ ደ/ታቦር እና ወረታ ከተማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ቢያንስ 200 ኩ/ል እና በላይ መጫን የሚችል መኪና ያለዉ እና የመኪናዉን የሊብሮ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ።
- ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን አይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል /በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-5 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የተመደበዉን ስኳር እና የምግብ ዘይት ሙሉ በሙሉ ማንሳት የሚችል፡፡
- አሸናፊዉ በተለየ በ5 ቀን ዉስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል፡
- ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ7ኛው በቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 7ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ወጭውን በመሸፈን በደ/ታቦር እና ወረታ ከተማ ከሚገኘው መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ መጋዘን ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከላይ የተጠቀሰዉ የስኳር እና የዘይት መጠን በተመለከተ የንግድና ገበያ ልማት ተቋም በሚያሳዉቀዉ መሰረት ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- የመጫረቻ ዋጋዉ ዉል ከተወሰደበት ቀን ጀምሮ ለ6 ተከታታይ ወራት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /0581419927 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደ/ታቦር ከተማ የመገናኛ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ.