በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
40

በምስ/ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አስ/ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተወዳዳሪዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጫረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋፋን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን 4፡15 ላይ ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 7 50.00 (ሀምሳ ብር) የማይመለስ በመክፈል መውሠድ ይችላሉ፡፡
  8. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ሰፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0586610002 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. መ/ቤቱ የሚገዙትን እቃዎች 20በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የሚገዙ እቃዎችን አሸናፊው ተቋሙ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
  15. የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስያዝ አለባቸው፡፡

 

ሞጣ ጤና አጠባባቅ ጣቢያ

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here