በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካይነት ለግብርና ጽ/ቤት በክልሉ ምክር ቤት ጸድቆ ቤቴን በራሴ እገነባለሁ በሚል መርህ የቀበሌ የገበሬ ማሰልጠኛ ተቋም በአ/አደር ሀብት ማሰባሰብ ይገንባ ተብሎ በተሰጠን አቅጣጫ መሰረት በጃንጓ ቀበሌ የጠበቀ የገበሬ ማሰልጠኛ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በምስራቅ ደምቢያ ገንዘብ ጽ/ቤት ከረዳት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ጥር 4/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 24/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኙ በፖስታ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅዶች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ22 ተኛው ቀን በተከታታይ ቀናት እስከ ጥር 25/2018 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጥር 25/2018 ዓ.ም በ22ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመከፍት ስልጣን አለው፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች (ተወዳዳሪ) አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ግንባታውን በፍጥነት ሰርቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ በሥራ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛውም ደረጃ በነበራቸው የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም፡፡
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

