በድጋሜ የወጣ ያገለገሉ እቃዎች  ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ብሄራዊ አባል የሆነ በህጻናት ደህንነት ጥበቃና ልማት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ከማንኛውም ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ እሳቤዎች ገለልተኛ የሆነ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ከተመሰረተበት እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት ፣ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ አዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ የሚገኝ የልማት አጋር ድርጅት ነው፡፡ ኤስ.ኦ.ኤስ የህጻናት መንደሮች  ባህር ዳር ፕሮግራም ያገለገሉ ላፕቶፕ ፣ኮምፒውተር ፣ኮፒ ማሽን ፣ፍሪጅ ፣ቴሌቪዥን ፣ኦቭን ፣ካሜራ ወንበር ፣ሸልፍ ወዘተ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡  ስለሆነም በጨረታው መወዳድር የሚፈልጉ ግለሰቦችንና ተቋማት ጨረታው ከወጣብት ቀን ጀምሮ  እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

  • ጨረታዉ ከሰኔ 30 ቀን 2017 ዓም እስከ ሃምሌ 10 ቀን 2017 ዓ/ም  8፡00 የሚቆይ  ሲሆን ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድና የሞሉብትን ዋጋ  በታሸገ ፖስታ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጅው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ጨረታው የሚከፈተው ሃምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሲሆን ተጫራቾችም ወይም ተወካዮቹ ባይኖሩም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • የመንግስት ታክሶች ፣ክፍያዎች እና የባለቤትነት ማስተላለፍ ክፍያዎች (ካለ) በገዥው ይሸፈናል፡፡
  • ተጫራቾች ሁሉንም ሎት ወይም የፈለጉትን ሎት ብቻ መርጠው ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በያንዳንዱ ሎት ሁሉንም እቃዎች ታሳቢ ያደረገ  ዋጋ  መሙላት የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚሞሎ ተወዳዳሪዎች ከተገኙ ከውድድሩ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሁሉም ሎቶች ብር 200 (ሁለት መቶ)  ብቻ ቢሮ ቁጥር 3 በመክፈል መዉሰድ  ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ጨረታዉን በሚያስገቡበት ጊዜ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ በባንከ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • አሽናፊ ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ5 ቀናት ውስጥ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሸናፊዎች በተጠቀሰዉ ቀን ዉስጥ  ካልከፈሉ  ድርጅቱ የራሱን አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ ባሉት በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የከፈሉበትን ዕቃ ማንሳት ያለባቸዉ ሲሆን በተሰጣቸዉ የጊዜ ገደብ የማያነሱ ተጫራቾች የከፈሉት ገንዘብና ንብረቱ /እቃዉ ወደ ድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
  • ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ  ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ

ሽምብጥ ቀበሌ ፣ካቶሊክ ታክሲ መጨረሻ ስልክ 058 226 49 70 /058 226 49 77 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር   ባሕር ዳር ፕሮግራም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here