በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
68

የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ቡድን ለቢቡኝ ወረዳ እንስሳት ዓሳ ሃብት ጽ/ቤት የእንስሳት መድሐኒት በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የግዥ ፈፃሚው እና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ  የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ/ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  6. የመድሀኒቱን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200 /ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የመድሀኒት አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ከ11/09/2017 ዓ.ም እስከ 25/09/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ16 ኛዉ ቀን በ26/09/2017 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከፊት ለፈቱ መፈረም አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 00 47 /49 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here