የአማራ ስቴት ዩንቨርሲቲ ድንኳን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በስቴት ዩንቨርስቲው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን/ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከጳጉሜ 03/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስቴት ዩኒቨርሲቲው የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በስቴት ዩንቨርሲቲው ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጳጉሜ 03/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 12/2018 ዓ.ም 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ መስከረም 12/2018 ዓ.ም 8፡00 ታሽጎ መስከረም 12/2018 ዓ/ም ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በስቴት ዩንቨርሲቲው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ስቴት ዩንቨርስቲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 2360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ስቴት ዩንቨርሲቲ